በአርባምንጭ ከተማ ትውልድ እና ዕድገቱን ያደረገው እና በአርባምንጭ ከተማ ከታዳጊ ክለብ አንስቶ እስከዋናው ቡድን ወጣትነቱን ለግሶ በመጫወት ያሳለፈውን ወጣት ስፖርተኛ ካጣን ቀናቶች ተቆጥረዋል።

በአርባምንጭ ከተማ ትውልድ እና ዕድገቱን ያደረገው እና በአርባምንጭ ከተማ ከታዳጊ ክለብ አንስቶ እስከዋናው ቡድን ወጣትነቱን ለግሶ በመጫወት ያሳለፈውን ወጣት ስፖርተኛ ካጣን ቀናቶች ተቆጥረዋል።

ሀዘኑ ከልብ የማይወጣ ለሀገር ብዙ ማገልገል በሚችለበት ጥሩ የወጣትነት ዕድሜ ላይ እርሱን እንደማጣታችን ለመርሳት የሚከብድ ትላቅ ሀዘንም እንደሀገር ገጥሞናል።

በነገው ዕለት በቀን 24/07/2016 ዓ/ም በአርባምንጭ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት አስተባባሪነት በትውልድ ከተማው አርባምንጭ ከተማ ሁለገብ ስታድየም እርሱን የሚዘክር የሻማ ማብራት ስነስርአት ከሰዓት 11:00 ጀምሮ ይካሔዳል።

በነገው ዕለትም የከተማችን ሕዝብ በነቂስ በመውጣት በስቴድየም በመገኘት ከወዳጅ ዘመዶቹ ጋር በመሆን ወጣቱን ትዘክሩ እና የሻማ ማብራት ስነስርአቱ ላይ ትገኙ ዘንድ ስፖርት ምክር ቤቱ ጥሪ ያቀርባል።

የአርባምንጭ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት!

Share this Post