የአርባ ምንጭ ሪፌራል ሆስፒታል በ2014 ዓ.ም በከፊል ሥራ እንደሚጀምር ተገለጸ።

የአርባ ምንጭ ሪፌራል ሆስፒታል በ2014 ዓ.ም በከፊል ሥራ እንደሚጀምር ተገለጸ።

የሆስፒታሉ ግንባታ 92% መድረሱም ታውቋል።

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ እና ልማት እቅድ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ታሪኳ ወልደመድህን የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ሊያ ታደሠ በግንባታ ላይ ያለዉን የአርባምንጭ ሪፌራል ሆስፒታል ጉብኝት አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቷ ዩኒቨርሰቲዉ በቀጣይ አመት በከፊል ስራ ለማስጀመር እቅድ ይዞ የሚኒስቴር መስርያ ቤቱን ድጋፍ የጠየቀ መሆኑን ገልፀዉ ሚኒስትሯም በጉብኝታቸዉ የህክምና ቁሶችን ለማስገባት ረጂ ድርጅቶችን ለማመቻቸት፣ በስልጠና እና የወጪ ድጋፍም ለማድረግ ቃል መግባታቸዉን አስረድተዋል።

ለማስጀመሪያ ዝግጅት የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ መቀጠሩን አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለማሟላት ኮሚቴ ተቋቁሞ እንቅስቃሴ መጀመሩንም ገልፀዋል።

አክለዉም በሆስፒታሉ ይዞታ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ምትክ ለመስጠት በቀበሌ ቤት ዉስጥ ላሉ ነዋሪዎች ከማዘጋጃ ቤት ጋር በመተባበር ተለዋጭ ቤት እየተሠራላቸዉ እንደሆነም አስረድተዋል።

Share this Post