13
Aug
2021
የአርባምንጭ ድል ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቀዶ ጥገናን ጨምሮ ሌሎች የህክምና አገልግሎቶችን በተሟላ መልኩ መስጠት መጀመሩ ተገለፀ።
በቅርቡ ሥራ የጀመረው አርባምንጭ ድል ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቀዶ ጥገናና ጨምሮ ሌሎች የህክምና አገልግሎቶችን በተሟላ መልኩ መስጠት መጀመሩን የሆስፒታሉ ዋና ሥራአስኪያጅ ስንሻዉ አበበ ገለጹ።
ሆስፒታሉ በቅርብ ጊዜ ከተመረቀ በኋላ በከተማ አስተዳደሩ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ማቴሪያልና የሰው ኃይል በማሟላት የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ መቆየቱን ዋና ሥራአስኪያጁ ተናግረው በትናንትናው ዕለት ከአርባምንጭ አጠቃላይ ሆሲፒታል ከመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር በመሆን የመጀመሪያ በቀዶ ጥገና እናቶችን የማዋለድ ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ሆስፒታሉ የጥርስ ህክምና አገልግሎት መስጠት መጀመሩና በቅርቡ የአይንና ሥነልቦና ህክምና እንደሚጀመር አቶ ስንሻው ተናግረዋል።
በሆስፒታሉ የድንገተኛ ቀዶ ጥገና ባለሙያ ያረድ ምንተስኖት ቀዶ ጥገና የተደረገበት ምክንያት የህጻኑ የልብ ምት ጥሩ ስላልነበረና በማህጸን ውስጥ ወፍራም ሆኖ መገኘቱን ገልጸው ከ40 ደቂቃ ቀዶ ጥገና በኋላ እናትየው ልጇን በሰላም ተገላገለች ብለዋል።