የአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የፋይናንስ አቅሙን ለማጠናከር ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ተካሄደ።

የአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የፋይናንስ አቅሙን ለማጠናከር ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ተካሄደ።

ክለቡን ለማጠናከር በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ከግልና ከመንግሥት ተቋማት፣ ከባለሃብቶች፣ ከነጋዴዎች፣ ከግለሰቦችና አጋር ድርጅቶች 16.5 ሚሊየን ብር ቃል መገባቱን የተናገሩት የአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ንጉሴ በቀጣይም ክለቡን ለማጠናከር ሁሉን የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ በሚያደርግ መልኩ የተለያዩ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር እንደሚያዘጋጅ ገልፀዋል።

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የክለቡ ቦርድ ፕሬዚዳንት የሆኑት ሰብስቤ ቡናቤ ክለቡን ባለበት ከፍታ ለማስቀጠል ቀደም ሲል የነበሩ ችግሮችን በማስወገድ ከብሔርና ከዘር ፖለቲካ ነጻ ሆኖ በብቃት፣ በቴክኒክና በስፖርት እንዲመራ በማድረግ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ ህዝባዊ መሠረት በማስያዝ ወደ ላቀ ከፍታ ሊሻገር ይገባል ብለዋል።

ክለቡ እስካሁን ህጋዊ ደጋፊ ማህበር ባለመኖሩ በበጎ ፈቃደኛ ድጋፊዎች መቆየቱን ተናግረው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ህጋዊ የክለቡ ደጋፊ ማህበር አባል በመሆን የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪያቸውን አስተላልፏል።

Share this Post