17
Nov
2021
በአርባምንጭ ከተማ በሁሉም ቀበሌያት የሚገኙ ሴቶች ለ5ኛ ዙር ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ100,000 / አንድ መቶ ሺህ ብር / በላይ በማሰባሰብ ስንቅና የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ ማድረጋቸውን የአርባምንጭ ከተማ ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት አሳውቋል።
ኢትዮጲያ ካለችበት ፈተና ለማሻገር በሚደረገው የህልውና ዘመቻ ከተማና አከባቢያቸውን ከመጠበቅ ባሻገር በግንባር ላለው ሀገር መከላከያ ሠራዊት በተለያየ መልኩ ድጋፍ መደረጉ የአንድነታችን መገለጫ ነው ያሉት የአርባምንጭ ከተማ ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ደመረ ናቸው።