01
Aug
2021
በ10 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የነጭ ሣር ብሔራዊ ፓርክ በዛሬው ዕለት በቀን 24/11/2013 ዓ/ም መመረቁን የፓርኩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስ ዘነበ ገልጸዋል።
ህንጻው ለተለያዩ አግልግሎት የሚውሉትን 19 ክፍሎችን የያዘ እንደሆነም ተገልጿል።
በዕለቱ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ አንድ አከባቢ ላይ መሠረተ ልማት ከተሟላ የትኛውንም ነገር ለመምራት አያዳግትም ያሉት ከቱሪዝም ጋር የሚገናኙ ሥራዎች ሁሉ ከመጠበቅ ባሻገር ወደ ሀገር ሀብት ለማድረግ የፓርኩ ጽ/ቤት መገንባት ትልቅ ትርጉም ይሰጣል ሲሉ ተናግረዋል።
ፓርኩ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎች እንዳይደርሱ በአግባቡ መጠበቅ እንዳለበትም አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዳይረክተር አቶ ኩመራ ዋቅጀራ በበኩላቸው የባለሥልጣኑ ዋና ቁልፍ ዓላማው የተፈጥሮ ሀብትን መንከባከብ፣የሰው ልጆች ኑሮ ህልውና ምቹ ማድረግ ነው ብለዋል።
ነጭ ሣር ብሔራዊ ፓርክ በልዩ ሁነታ ድጋፍ ተሰጥቶ ጥበቃውም የተጠናከረ መሆን እንዳለበትና በፓርኩ ዙሪያ ያሉ ተግዳሮቶችን በጋራ መሥራት ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል።