የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ፐብልክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በዕቅድ አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማትና ፈጻሚዎች የዕውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ።
የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ፐብልክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታፌ ታደሰ የፐብልክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት በአስር ዓመቱ ስትራቴጅክ ዘመን ተልዕኮ በወሰዳቸው ሦሥት የትኩረት መስኮች ማለትም የማስፈጸም አቅም ግንባታ፣በመልካም አስተዳደርና ህብረተሰብ ተሳትፎ እና በሰው ሀብት አመራር ሥርዓት የተሰጠውን መንግሥታዊ ተልዕኮ እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።
በ2013 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደር ሥር ከሚገኙ መስሪያ ቤቶች አፈጻጸም የላቄ ውጤት ያስመዘገቡ ፈጻሚዎች ወንድ 54 ሴት 26 በድምሩ 80 ከሴክተሮች 1ኛ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት 2ኛ ውሃና ፈሳሽ አገልግሎት 3ኛ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት እንደሆኑ ተናግረው ተሸላሚ ተቋማትና ሠራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ በከተማው በርካታ የልማት ሥራዎች መሠራት እንደተቻለና ለዚሁ የመንግሥት ሠራተኞች አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ዛሬ የሚደረገው የዕውቅናና ሽልማት አሰጣጥ መድረክ ቀጣይ ላይ ዕቅድ ታቅደው በተደራጀ ሀይል ተግባራትን እያሳካን የፐብሊክ ሰርቪሱን እውቅና እየሰጠን ለሚንሄድበት የተሻለ መነሻ እንደሆነና ለቀጣይ 2014 በጀት ዓመት ሴክተሩና ፈጻሚው የተሻለ አፈጻጸም እንድያመጣ የሚያበረታታ ነው ሲሉ ከንቲባው ተናግረዋል።
የጋሞ ዞን ፐብልክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መኮንን ቦራጎ ፐብልክ ሰርቪስ ጽ/ቤት በሴክተሩና ፈጻሚው ላይ ያደረገው ምዘና ጥያቄ በማያስነሳ መልኩ ተመዝኖ መቅረቡ ሊደነቅ ይገባል፡መድረኩ ለሌሎች ወረዳዎችና ከተሞች ጥሩ ተሞክሮ የሚሆን ነው ዕወቅና ሊሰጠው ይገበዋል ሲሉ ተናግረዋል።