01
Aug
2021
በጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ ኢትዮጵያን እናልብስ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃግብር ተካሄደ።
የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በመርሃግብሩ ተገኝተው እንደተናገሩት በአንድ ጀምበር 10 ሚሊየን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃግብር ህብረተሰቡ ችግኝ መትከልና መንከባከብ ባህሉ በማድረግ እየሰራ መሆኑን ተናግረው፡ ከተማችን ለምለምና የምድር ገነት መሆኗን ለማስቀጠል የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ሊጠናከሩ ይገባል ብለዋል።
የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ በበኩላቸው በዛሬው ቀን ከ80 ሺህ በላይ ችግኞች በተመረጡ ቦታዎች መተከላቸውን ገልጸው፡ ህብረተሰቡ የተከለውን ችግኝ በትኩረት በመንከባከብ ማጽደቅ እንዳለበትና ከተመረጡ ቦታዎች ባሻገር በትምህርት ቤቶችና በየደጁ ችግኞች ሊተክሉ እንደሚገባም ተናግረዋል።