በአርባምንጭ ከተማ "ለከነማዬ እሮጣለሁ" በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ።

የአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የፋይናንስ አቅም ለማጠናከር "ለከነማዬ እሮጣለሁ" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ የከተማው ነዋሪዎች እና የክለቡ ደጋፊዎች በነቂስ በመውጣት በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።

የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የክለቡ የበላይ ጠባቂ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ዘውዴ እና የአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ፕሬዝዳንት እና የከተማው ከንቲባ የሆኑት ሰብስቤ ቡናቤ በመርሃግብሩ በመገኘት ክለቡን ለማጠናከር በተደረገው ለተሳተፉ የከተማው ነዋሪዎች፣ ለክለቡ ደጋፊዎች፣ ለጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ አባላትና ደጋፊዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Share this Post