17
Nov
2021
ምዕራባዊያን ሀገራት አሜሪካንን ጨምሮ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ የያዙት አቋም እና ሚዲያዎቻቸው የሚያሰተላልፉት ዘገባ ከእዉነት የራቀ ነዉ ሲሉ ከአሜሪካ የመጡ ሚሶናዊያን ተናገሩ።
የአሜሪካ ዜጐች አርባ ምንጭ ዓላም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናትና የሀገር የሽማግሌዎች ደማቅ አቀባበል አድርገዉላቸዋል።
70 አባላትን የያዘው የአሜሪካ ዜጎች ቡድን ወደ ኢትዮጵያ የመጣዉ የሚሽን ጂሰስ ፎር ሚኒስትሪ በተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ደስተኞች መሆናቸውን በመግለፅ ከእዉነት የራቁ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላት እዉነትን ካለመፈለግ የመነጨ ስለሆነ በዉጭ ሀገራት ለሚገኙ ሁሉ ኢትዮጵያ አሁን እጅግ ሰላማዊ መሆንዋን ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማወቅ አለበት ያሉት የሚሽን ጂሰስ ሚኒስትሪ መስራችና ባለቤት አንድሬ ሻፕቫሌ ግልፀዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ መምጣቷን የሚትገልፀዉ የማህበሩ አባል ባየችዉ ነገር እጅግ ደስተኛ መሆኑዋን በመግለፅ አዲስ አበባን ጨምሮ አርባምንጭ ለደህንነታቸው የሚያሰጋ አንድም ነገር እንዳላጋጠማቸው ትናገራለች።