03
Apr
2024
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሁለተኛ ዙር 18ኛ ሳምንት ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ አቻውን የደሴ ከተማ እግርኳስ ቡድንን አሸነፈ
***********
አርባ ምንጭ፣ መጋቢት 25፣ 2016 ዓ፣ም (የአርባምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን )
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሁለተኛ ዙር 18ኛ ሳምንት ጨዋታውን በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲዬም በ7፡00 ሰዓት ከደሴ ከተማ እግርኳስ ቡድን ጋር ያደረገው አርባምንጭ ከተማ 5ለ 1 በሆነ ውጤት አሸናፊ ሆኗል።
የአርባምንጭ ከተማ እግርኳስ ክለብ የወንዶች ቡድን ክለብ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሁለተኛ ዙር ያደረጋቸውን አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች በማሸነፍ በከፍተኛ ሊግ ምድብ "ለ"ን በ48 ነጥብ እየመራ ይገኛል።
አርባምንጭ ከተማ እግርኳስ ክለብ