03
Apr
2024
በአርባምንጭ ከተማ የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል
ከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ውበት ለማስጠበቅ በ2016 በጀት ዓመት ከ201 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
አርባምንጭ፡መጋቢት 25/2017 ዓ/ም (አርባምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን)
ከተማ አስተዳደሩ በተያዘው 2016 በበጀት ዓመት በከተማው በተመረጡ ቦታዎች ኮብል ድንጋይ ንጣፍ 5.4 ኪ.ሜ.፣መንገድ ዳር አረንጓደ 3.2 ኪ.ሜ፣ሪተይንግ ወል፣ትራንስፎርመር፣ካልቨርት እና ሌሎችን ከ201 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
የመንገድ ዳርቻ አረንጓደ ልማት ሥራ እና ሌሎች ግንባታዎች ለከተማዋ አድስ ገጽታ ለነዋሪቿና እንግዶቿ ምቹና ተስማሚ የማረፊያ ሥፍራን ስለሚፈጥር በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስተዳደሩ አሳውቋል።
እየተገነቡ ያሉ መሠረተ ልማቶች ለከተማው ውበት ከመስጠት ባሻገር ለብዙ ሰዎች ሥራ ዕድል እንደፈጠረላቸው ተገልጿል።
የተጀመሩ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ክትትል ይደረጋል።
የተሠሩ መሠረተ ልማቶችን ማህበረሰቡ የኔ ነው በማለት ሊንከባከበውና ሊጠብቀው እንደሚገባ ከተማ አስተዳደሩ አሳስበዋል።