የአርባምንጭ ከተማ ሴቶች ከ100,000 / አንድ መቶ ሺህ/ ብር በላይ አሰባስበው ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ስንቅ በማዘጋጀት አጋርነታቸውን አሳዩ።

በአርባምንጭ ከተማ በሁሉም ቀበሌያት የሚገኙ ሴቶች ለ5ኛ ዙር ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ100,000 / አንድ መቶ ሺህ ብር / በላይ በማሰባሰብ ስንቅና የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ ማድረጋቸውን የአርባምንጭ ከተማ ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት አሳውቋል።

ኢትዮጲያ ካለችበት ፈተና ለማሻገር በሚደረገው የህልውና ዘመቻ ከተማና አከባቢያቸውን ከመጠበቅ ባሻገር በግንባር ላለው ሀገር መከላከያ ሠራዊት በተለያየ መልኩ ድጋፍ መደረጉ የአንድነታችን መገለጫ ነው ያሉት የአርባምንጭ ከተማ ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ደመረ ናቸው።

Share this Post